የቨርጂኒያ 3-ቀን የሽያጭ ታክስ በዓል | ኦገስት 1-3 ፣ 2025 

መቼ ነው? 

ኦገስት 1 - 3 ፣ 2025 3 -ቀን የሽያጭ ታክስ በዓላት በነሐሴ ወር የመጀመሪያው አርብ በ 12 01 am ላይ ይጀምር እና በሚቀጥለው እሁድ በ 11 : 59 pm ላይ ያበቃል።

ምንድነው ይሄ፧  

በሽያጭ ታክስ በዓላት ወቅት፣ የሽያጭ ታክስ ሳይከፍሉ ብቁ የሆኑ የትምህርት ቤት አቅርቦቶችን፣ አልባሳት፣ ጫማዎችን፣ አውሎ ንፋስ እና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ዕቃዎችን እና የኢነርጂ ስታር ™ እና የዋተር ሴንስ ™ ምርቶችን መግዛት ይችላሉ።

ብቁ የሆኑት ዕቃዎች የትኞቹ ናቸው?

ብቁ የሆኑ ዕቃዎች ዝርዝር እና ለቸርቻሪዎች ተጨማሪ መረጃ በሽያጭ ታክስ የበዓል መመሪያዎች ውስጥ ይገኛሉ።